Wednesday, August 13, 2008

በሀረሪ ሕዝብ ክልል ዘንድሮ 71 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወሰዱ

ሐረር, ነሐሴ 7 ቀን 2000 (ሀረር) - በሐረሪ ሕዝብ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ206 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ መነሻ ካፒታል ያስመዘገቡ 71 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ስራ መጀመራቸውን የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ገለጠ፡፡

የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር አቶ ጥበቡ አይፍረስ ትናንት ለኢዜአ እንደገለጡት ፈቃድ የወሰዱት ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ በሪልስቴት በግብርና በኮንሰትራክሽን በትምህርት በጤና በማእድንና በሌሎችም አገልግሎት መስጫ ተቋማት ነው፡፡

ባለሀብቶቹ በግንባታ ላይ መሆናቸውን አስታውቀው ማምረትና አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩ ከስድስት መቶ ለሚበልጡ ወገኖች የስራ አድል እንደሚፈጥሩ ገልጠዋል፡፡

በክልሉ በበጀት ዓመቱ የኢንቨስትመነት ፈቃድ የወሰዱት ባለሀብቶች ካለፈው ዓመት በእጥፍ እድገት ማሳየቱን ገልጠው የሚሊንየሙና የሀረር ከተማ ምስረታ በዓል ለኢንቨስትመንት መጨመር አስተዋጸኦ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡

የክልሉ ኢንቨስትመንት ጽሕፈት ቤት አዋጪ ፕሮጀክቶችን በማጥናት ለባለሀብቶች የማስተዋወቅ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጠዋል፡፡

በክልሉ የተሟላና ቀልጣፋ መስተንግዶ ያለ በመሆኑ ባለሀብቶች በሚፈልጉት የስራ መስክ ወደ ክልሉ በመምጣት ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሪፖያ ኤዲ2 3፣00

---END---

No comments: